አቡነ ዜና ማርቆስ በ 12ኛ መቶ ክ/ዘመን የነበሩ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ናቸው።
በተለያዩ የሀገሪቱ ክፈሎች እየተዘዋወሩ ሥራን፣ ፍቅርን፣ መረዳዳትንና በሥርዓት መኖርን በማስተማር በተጨማሪም ብሔር፣ ሃይማኖትና ወገን ሳይለዩ ለተቸገረ በመርዳት በማኅበረሰቡ ውስጥ ፍቅርን በማሳየት አርአያ ሆነዋል።
ዕቁብ የተባለውን ባሕላዊ የገንዘብ ቁጠባ ዘዴን በመጀመርና በማስፋፋት ወገን ከወገኑ ጋር እንዴት ማደግ እንደሚችል አሳይተዋል። ለሀገርና ለወገን መልካም ያደረጉትን ለማዘከርና አርኣያነታቸውን ለመከተል በማሰብ የዚህ ማኅበር ስያሜ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብሏል።
ለችግር የተጋለጡ ህጻናትና አረጋውያን ሁለንተናዊ አቅማቸው ጎልብቶ ለማኅበረሰቡ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ ማየት
ወገን ለወገኑ የሚደርስበትን ባህል በማዳበር ከቤተሰቦች፣ ከማኅበረሰቡና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለችግር የተጋለጡ ህጻናትና አረጋውያን ሙሉ ድጋፍ አግኝተው ሁለንተናዊ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ማስቻል